Saturday, November 21, 2015

በትግራይ ምእራባዊ ዞን እየተካሄደ ባለው የህዝብና የአስተዳደሮች ስብሰባ የዞኑ ምክትል አስተዳደር በሙስና ምክንያት ከስራ ዘርፉ እንደተባረረ ከቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን እየተካሄደ ባለው የህዝብና የአስተዳደሮች ስብሰባ የዞኑ ምክትል አሰተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ወልደስላሴ የተባለው ሰዉ ስልጣኑን ተገን በማድረግ ከህዝባዊ ሃላፊነት ውጭ ርካሽ በሁኑ ስራዎች ለግል ጥቅሙ እንደተሰማራ በተሰብሳቢው ህዝብ በቀረበበት ማስረጃ ከስራው እንደተባረረ ለማወቅ ተችሏል።
       በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁት ባለ ስልጣኑ በህዝቡ ዘንድ ሲገመገም በሙስና ተዘፍቆ ለተለያዩ ችግሮች አጋልጦናል የሚሉና ሌሎች ሂሶች ጥቅምት 22/2008 ዓ/ም በተካሄደው የግምገማ ስብሰባ ሂስ ቀርቦለት ከስራው እንደተባረረ ከገለፀ በኋላ አሁንም የሰብሰባው ግምገማ በሰፊው እየቀጠለ እንደሚገኝ መረጃው አስረድቷል።