Saturday, November 21, 2015

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ውስጥ የሚገኝ እስር ቤት ከ 3 ሺ በላይ እስረኞች በመያዙ ምክንያት እስርቤቱ ከአቅሙ በላይ ሁኖበት እንደሚገኝ ታወቀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኝ እስር ቤት ከ 3 ሺ በላይ እስረኖች በመያዙ ምክንያት እስርቤቱ ከልኩ በላይ ሁኖበት እንደተጨናነቀ በከተማው የሚገኙ ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
        በመሆኑም እስር ቤቱ ከአቅሙ በላይ እስረኞች በመያዙ የተነሳ ቤቶቹ ቀን በቀን የሚገባው የእስረኛ ቁጥር ሊያስተናግዱ ስላልቻሉ ተጨማሪ ቤቶች በቆርቆሮ ሰርተው እስረኞቹ እያጎርዋቸው እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።