Wednesday, November 11, 2015

በትግራይ ክልል እስር ቤቶች ፍርደኛ ተብለው ታጉረው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ዜጎች አብዛኛዎቹ ወንጀል የሌላቸው የፖለቲካ እስረኞች እንደሆኑ ተገለፀ።



         ያለ ህዝባዊ ውክልና በስልጣን ላይ የሚገኘው የገዢው ሕወሓት/ኢህአዴግ ጉጅሌ በየመድረኮችና በየሚድያዎቹ በዴሞክራሲያዊ ስርአታችን ፍትህ ነግሰዋል በማለት የሚነዛው የአሉባልታ ወሬ ለህዝባችን እሬት እየጣመው ነው በማለት የገለፀው መረጃው በመሆኑም በትግራይ ክልል እስር ቤቶች ታጉረው እየተሰቃዩ ያሉትን ወጣት እስረኞች  የስርአቱ ካድሬዎች በጠብ ተነሳስተው ያለ ምንም ህጋዊ ማስረጃ “ ይመስላል" ና “ ይሆናል“ በሚሉ ቃላቶች በመደርደር ስለ ሚከሷቸው ብቻ እስራት የተፈረደባቸው እንደሆኑ ተጎጅዎችን መሰረት በማድረግ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችልዋል።
        መረጃው ጨምሮ። በየእስር ቤቱ ህጋዊነት ያለው የእስረኛ አያያዝ ካለመኖሩ የተነሳ በርከት ያሉት እስረኞች በደህንነትና በፖሊሶች በለሊት እየተጠሩ በመገረፍ ላይ እንደሚገኙና በአስቃቂ ግርፋት ህይወቱን ያጣ ደግሞ ቦታው ተቀየረ በማለት ለቤተሰቡ ምላሽ ስለ ሚሰጧቸው የልጆቹ ወላጆች  ደግሞ ልጆቻቸውን ለማግኘት ከቦታ ወደ ቦታ ለመንከራተት እየተገደዱ እንደሚገኙ ተገለፀ።
         በመጨረሻም በመቐለ እስር ቤት ከ4 ሺ በላይ እስረኞች የሚገኙ ሲሆኑ ለነዚህም የሚበቃ ንፁህ  የመጠጥና የማጠቢያ ውሃ ካለመኖሩ የተነሳ እስረኛው ውሃ በማለት የሚውልበትና የሚያድርበት ሰአት እንደሚበዛ የገለፀው መረጃው የስርአቱ ባለ ስልጣናት መጥቶዉ ባሚያድርጉት ስብሰባ ላይም ችግራቸውን እንዲፈታላቸው የተናገሩ ቢሆኑም እንኳ በሃላፊዎቹ በኩል ከፕሮፖጋንዳ ባለፈ ግብራዊ የሆነ መፍትሄ እንዳላስቀመጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።