Saturday, December 29, 2012

በአማራ ክልል ፤ ምእራብ ጎጃም ዞን ፤ ወንበርማ ወረዳ ፤ በሽለንዲ ከተማ በሚገኘው የወ/ሮ አታለል ሻይ ቤት ውስጥ አቶ ይሁን ደምመላሽ የተባለ ንጹህ ዜጋ በኢህአደግ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደሉን ቷውቋል።

አቶ ይሁን ደምመላሽ በታህሳስ 11,2005 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጭንቅላቱ ላይ በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ ያለፈው ፤ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች አባላት ክንዴ ይርሁ ፤ ደሳለኝ ማሞ ፤ ኮንስታብል ለአለምና ሌላ ለግዜው ስሙ ያልታወቀ አራተኛ ግለሰብ በተተኮሰበት ጥይት መሆኑ በቁጭ ወረዳ ፤ ከአሰስ ወይንማ ቀበሌ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ባለፈው ሳምንት የከተማዋ ኗሪዎች ጉዳዩን ወደ እሚመለከተው የክልል ባለስልጣናት ለማቅረብ 8 አባላት ያሉት አንድ ኮሞቴ አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።