Saturday, December 29, 2012

እያወዛገበ ባለው የሞስሊም መካነ መቃብር ጉዳይ ለመነጋገር የምስራቃዊ ዞን አመራሮች የጸጥታና የፖሊስ ሃላፊዎች በዓዲ-ግራት ከተማ በስብሰባ ላይ መሆናቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

-->


መንግስት 40 ሚልዮን ብርና ተለዋጭ ቦታ በመስጠት በምትኩ መካነ መቃብሩ ተነስቶ ቦታውን እንዲረከብ ጥያቄ አቅርቧል ። የሞስሊሙ ማህበረሰብ በበኩሉ ከመጀመሪያውኑ እኛን ሳታማክሩ መካነ መቃብሩን በመድፈር አራክሳችሁ ስታበቁ አሁን እንዲህ ዓይነቱ ገንዘብ ተቀበሉ ማለታችሁ በሃይማኖታችን ሓራም ስለሆነ አሳዝኖናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ በዓዲ-ግራት ከተማ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ አንድ የዓፋር ተወላጅ ሞስሊም ወገናችን የቀብር ስነስርዓት በከተማዋ የሚገኝውን የሞስሊም መካነ መቃብር ተራክሷል በሚል ምክንያት ዕዳጋ ሓሙስ ከተማ በሚገኝው የሞስሊም መካነ መቃብር እንዲፈጸም መደረጉ ቷውቋል።
በአሁኑ ግዜ በዓዲ-ግራት ከተማ የሚገኘው የሞስሊም መካነ መቃብር በፈዴራል ፖሊስ ጥበቃ ስር ነው ። የዞኑ አመራሮች በመካነ መቃብሩ ውስጥ ጠላት ፈንጅ እንዳይቀብር ለመከላከል የሚደረግ ጥበቃ መሆኑ በማስመሰል ህዝቡም ለማምታታት ቢሞክሩም ፤ ዋናው ምክንያት ግን የሞስሊሙን ማህበረሰብ ተቃውሞ ይነሳል ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑና በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ከተሞችም ጭምር በፌደራል ፖሊስ አባላት የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣