Friday, January 4, 2013

በሽሬ እንዳስላሴ ፤ በሰለኽለኻና በእንዳባጉና ከተማ ከታህሳስ 21/2005 ዓ/ም ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የፖሊስ አባላትን እንቅስቃሴ የሚመለከት ህዝባዊ ግምገማ ኗሪው ህዝብ በስርዓቱ የፖሊስ ሃይል ላይ እምነት እንደሌለው ገለጸ።

በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖሊስ አባላት ህዝቡን በቅንነት ከማገልገል ይልቅ ለስርዓቱ ባለስልጣናትና ገንዘብ ላላቸው ግለሰቦች የቆሙ በመሆናቸው ህዝባዊ ፖሊስ አለ ብሎ ለማለት አይቻልም፥ ፖሊስ  ሃላፊነት የማይሰማው በጉቦና አድልዎ የሚሰራ የአንድ ድርጅትና የጥቂት ግለሰቦች አገልጋይ ነው ቢባል ይቀላል ሲሉ የሦስቱ ከተሞች ኗሪዎች በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።
ይህ በእንዱህ እያለ በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖሊስ ሃላፊዎች ከታህሳስ 21,2005 ዓ/ም ጀምሮ በየዞናቸው የ 6 ወር የስራ ግምገማ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።