Thursday, January 3, 2013

በሸራሮ ከተማ በሙሴ አዳራሽ ታህሳስ 21,2005 ዓ/ም ጥላሁን በርሀ በተባለ ካድሬ የተመራ ስብሰባ ያለውጤት መበተኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

በደረሰን ዘገባ መሰረት ካድሬው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለተሰብሳቢው ለማቅረብ ቢሞክርም የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ግን የከተማዋን የውሃ እጥረት ለማቃለል በሚል የተመደበው ገንዘብ የት ገባ? ቅድሚያ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው የሚል ጥያቄ በማንሳት ካድሬውን ወጥረው እንደያዙት ቷውቋል።
መንግስት ለከተማዋ የውሃ እጥረት ቱክረት ሰጥቶ ለመፍታት ስላልተንቀሳቀሰ በአንድ ቦቲ የመጣውን ውሃ ለከተማዋ ኗሪ ህዝብ በሙሉ ማዳረስ አልተቻለም። የተገኘውንም ቢሆን በአግባብ ስለማይከፋፈል ፍትሃዊነት ይጎድለዋል ሲሉ የከተማዋ ኗሪዎች ይናገራሉ።
የከተማዋን የውሃ እጥረት ለማቃለል ለውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተብሎ የተያዘ በጀት የት እንደገባ ሳይታወቅ ፤ ኗሪው በውሃ እጥረት እየተቸገረ ባለበት ሁኔታ ከአቅማችን በላይ የሆነ ፍትሃዊነት የጎደለው የግብር አከፋፈል ምክንያት በደል እየደረሰብን ነው በማለት በአደራሹ የተገኙ ኗሪዎች ምሬታቸውን ገልፀዋል።
ህዳር 8,2005 ዓ/ም በጥላሁን በርሀ የተመራ ስለ ግብር አከፋፈል የተመለከተ በሸራሮ ከተማ የተደረገ ስብሰባ ግብር ከፋዩ ህዝብ አሁን ባለው የዋጋ ንረትና የአቅርቦት እጥረት ከአቅማችን በላይ የሆነ ግብር መክፈል አንችልም ሲል መቃወሙ የሚታወስ ነው።