Tuesday, January 8, 2013

በትግራይ ክልል ኦዲትና ፋይናንስ የተመራ በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ፤ ‘በገባር ሽረ ሆቴል’ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደ ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቀቀ።

የዞን ሃላፊዎች ፤ የወረዳዎች አስተዳደሮችና የሴክተር ሃላፊዎች እንደዚሁም የጣብያ ሃላፊዎችና ስራ አስከያጆች በስብሰባው የተገኙ ሲሆን አንዳንድ የህዝብ ወገንተኝነት የሚሰማቸው ግለሰቦች የህዝቡን ስሜት በስብሰባው ለማንጸባረቅ ቢሞክሩም ከመድረኩ አመራር ማስጠንቀቅያ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችለዋል።
ከክልል የተላከው ቡድን ይዟቸው የመጣ 7 አጀንዳዎች፣
1-     በመንግስት ታቅደው ተግባር ላይ ሳይውሉ የቀሩ እቅዶች በህዝቡ ዘንድ የፈጠሩት ስሜት ምን ይመስላል? ክህዝቡ ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል።።
2-     መልካም አተዳደርን በተመለከተ በህዝቡ የሚታዩ ቅሬታዎች የሚመለከታቸው አካላት እንዴት ይገመግሙታል።
3-     ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለው እምነት ምን ይመስላል?
4-     በወረዳና በጣብያ በሚደረግ ምርጫ ህዝቡ እንዴት ሊቀበለን ይችላል ?
5-     ግብርን በተመለከተ ቅሬታዎች አሉ። ህዝቡ በምን መልኩ ነው የተረዳው ? የሚመለከታቸው አካላትስ በምን መልኩ ነው ያስረዱት?
6-     ጸጥታን በሚመለከት ጸጥታ ማስከበር የሚገባቸው የፖሊስ አባላትና ታጣቂዎች ወደ ግል ስራቸው ሲያተኩሩ ይታያሉ ፥ የመንግስትን ስራ ለማን እየተውለት ነው?
7-     ሁላችንም እንደምናውቀው ህዝብ ርቆናል፥ አሁን ክህዝቡ ጋር እንዴት መቀራረብ እንችላለን?
የሚሉ ነጥቦችን በአጀንዳው የተነሱ ሲሆን በስብሰባው ከተገኙት የህዝብ ወገንተኝነት የሚሰማቸው ተሰብሳቢዎች እንዳልተቀበሉት ከስብሰባው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
የህወሓት ካድሬዎች የማይተገብሩት ቃል በምግባት የትግራይን ህዝብ እያታለሉ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም ቢሞክሩም የሰሜን ምዕራብ ትግራ ግን እናንተ የተግባር ሰዎች አይደላችሁም ፥ ማምታታት ይብቃ ፥ በማለት ተቃውመውን ከክልል ለተላከው ቡድን በግልጽ አንጸባርቋል።
ተሰብሳቢዎቹ በማያያዝ በክልል በተዋረድ በሃላፊነት ቦታ የተቀመጣችሁ ሁላችሁም ተጠያቂነት ብሎ ነገር አታውቁትም፣ በሙስና የበሰበሳችሁ በመሆናችሁ ፤ እጅ ከፈንጅ የተያዙትን ሙሰኞችንም ቢሆን ስታበረታቱ እንጂ ወደ ህግ ስታቀርቡ አትታዩም ። ለአብነት የታሕታይ አድያቦ አስተዳደር የነበረ አብራሃለይ አበራና የገጠር ልማት ሃላፊ የነበረ አለም ግዴና ከ 300 ሺ ብር በላይ የህዝብ ገንዘብ ለመዝረፋቸው ተጨባጭ ማስረጃ ቀርቦላቸው እያለ ወንጀሎኞችን ወደ ህግ እንዲቀርቡ አልተደረገም ፥ ይልቁንም  ወደ ሌላ ቦታ ተዛውረው እዲሰሩ ተደረገ። ይህ በስርዓቱ ውስጥ የተሰራፋውን የሙስና ኔት ወርክን በጋህድ የሚያሳይ ነው ሲሉ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በምሬት ገልጸዋል።