Friday, January 4, 2013

በአዊ ዞን ፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ስራ አቆሙ።

በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተሰማሩ ነጋዴዎች የኢህአደግ መንግስት ኢፍትሃዊ የግብር አከፋፈል ስርዓትን በመቃወም ከታህሳስ 22,2005 ዓ/ም ጀምሮ ስራ አቁመዋል። በመካሄድ ላይ ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ በአከባቢው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት ተከስቷል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት በአከባቢው የተሰማሩ የፈዴራል ፖሊስ አባላት ከፍላጎት ውጭ ባለንብረቶችን በማስገደድ ተሽከርካሪዎችን ለማሰማራት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።