Friday, April 12, 2013

በትህዴን ሬድዮ የሚተላለፈው ፤ በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ፤ መንግስት የሚያካሂደውን እንቅስቃሴን የተመለከተ ዘገባ እንዴት ሊደርሰው ቻለ የሚል ግምገማ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ መካሄዱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊ ወዲ-ሻምበል የተመራ ስብሰባ ሚያዝያ 01/ 2005 ዓ/ም ረፋድ ላይ የከተማዋ ኗሪዎች ተወካዮችና የመስተዳድር አካላትን እንደዚሁም ከሰዓት ብሁዋላ በከተማዋ የሚገኙ የዞን ፖሊስ ጽ/ቤትና የከተማዋ የፖሊስ አካላት በተገኙበት ጸጥታን የተመለከተ ግምገማ ቢደረግም የተገኘ ውጤት ግን የለም፣
በስብሰባው በማሃከላችን ያለው የስራ ግንኝነት ምን ይመስላል? በፖሊስ አባላት ይሁን በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ተጨባች ሁኔታ ምን ይመስላል? በትህዴን ሬድዮ እየተላለፈ ያለው የመንግስት ተግባራትን የሚያጋልጥ ዘገባ እንዴት ሊደርሰው ቻለ? የሚሉና ሌሎች ጭንቀት የወለዳቸው ጥያቄዎችን በስብሰባው የቀረቡ ሲሆን በተለይም ትህዴን በሚድያው እያስተላለፈው ያለ መንግስት በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የተመለከተ ዘገባ እያቀበለው ያለ ማን ነው? ተጠርጣሪውን አውጡት ካልሆነ እናንተው ናችሁ የሚል ግምገማ በማቅረብ ተሰብሳቢዎችን ውጥረት ውስጥ ማስገባቱን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣
    በተለይም ኮንስታብል ሽሻይ ስለ ተባለ መርማሪ ፖሊስ የሚመለከት በትህዴን ሬድዮ የተላለፈ ዘገባ በተያያዘ ትህዴን ዘገባውን ልቅም አድርጎ ማቅረብ የቻለው አንተው እራስህ ስለሰጣሃቸው ነው ወይም የነገርካቸው ሰዎች ካሉ አቅርብ ካልሆነ ከዚህ ቀደም ከተወሰነብህ ቅጣት በተጨማሪ አሁንም አስፈላጊ እርምጃ እንደሚወሰድብህ እንድታውቅ ይገባል በማለት የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቡን ለማስፈራራት እንደሞከረ ለማወቅ ተችለዋል፣