Friday, April 12, 2013

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በከፋ ዞን ፤ በጫና ወረዳ የቅንጅት አመራር አባላት የኢህአዴግ ስርዓት በሚፈጥረው መሰናክል ምክንያት የምርጫ ቅስቀሳን ማድረግ መቸገራቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት የቅንጅት አባላት ከቀናት ብሁዋላ በሚደረገው የከተማና የአከባቢ ምርጫ ለመሳተፍና ህዝቡን ለመቀስቀስ ከ አ/አ ከተማ ወደ ጫና ወረዳ መጋቤት 27/2005 ዓ/ም በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት የዞኑ ሃላፊዎች ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት በአከባቢው የስርዓቱ አባላት የሆኑ ወጣቶች በማሰማራት የቅንጅትን አባላት በድንጋይ እንዲደበደቡ የተደረገ ሲሆን ከፓርቲው አባላት መካከል አቶ ጣቃ ገ/ሚካኤል ገብረ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፣
በተመሳሳይ በአከባቢው የሚገኙትን የቅንጅት አባላትን ደን ጨፍጭፋችሃል በሚል ሰበብ የአከባቢው የፖሊስ ሃይል እየተያዙ ያለምንም ማስረጃ እንደ ወንጀለኛ እየታሰሩ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
በከፋ ዞን ቅንጅትን ወክለው ለመወዳደር የተመዘገቡ እጭዎች
1-አቶ አስራት ታየ
2-አቶ ደመቀ መኮንን
3-አቶ አቤል አሰይ ይማም
4-ወ/ሮ መሰለች ጓንጉል
5-አቶ ወ/ማሪያም ሳኔ
ሲሆኑ የፓርቲው አባላት የሚያደርጉትን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግበትና የተለያዩ በደልም እንደደረሰባቸው ቷውቋል፣
ኢህአዴግን ወክለው በዞኑ ለመወዳደር የተመዘገቡ እጭዎች
1-አቶ መሰለ ከበደ
2-ወ/ሮ አልማዝ ወንድማገኝ
3-አቶ ገ/ሚካኤል ወ/ጅወርጊስ
4-አቶ ተመስገን ተካ
5-ወ/ሮ አባይ ነሽ ወ/ሚካኤል
መሆናቸውንም ዘገባው ገልጾ እነዚህን ያልመረጠ ኗሪ ወየለት በማለት የስርዓቱ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ሰውን እያስፈራሩት መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፣