Friday, April 12, 2013

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጋሞጎፋ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ፣



በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ የመንግት መ/ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ባደረጉበት ወቅት ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በማቋረጥ ሰራተኛውን በመደገፍ ተቋውማቸውን ገጸዋል፣
በተቋውሞው ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል መብታችን ይከበር ? ሃይማኖታችን ይከበር ? በቋንቋችን የመማር እድል ይሰጠን የሚሉ ይገኙባቸዋል ፣
የመንግስት ሰራተኞቹ ከመካከላቸው አራት ሰዎችን በመወከል ጉዳያቸውን ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት እንዲያቀርቡ የላኩ ቢሆንም ተወካዮቹ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው እንደታሰሩ ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በባህርዳር ከተማና አከባቢዋ ተቃውሞ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት ያደረበት የኢህ አዴግ ስርዓት ከብርሸለቆ ተመርቀው የወጡ ወታደሮችን በ 27 አውቶብሶች በመጫን በባህዳር ከተማና አከባቢዋ በጥበቃ እንዲሰማሩ ማድረጉን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ፣