Friday, April 12, 2013

የሸራሮ ከተማ ኗሪ ህዝብ ገዥው ፓርቲ ብቻውን የሚወዳደርበት ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሊሆን አይችልም በማለት ተቃውመውን ገለጸ፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ከተማዋ የተላኩ ካድሬዎች የከተማዋን ኗሪ ህዝብ ከመጋቢት 28,2005 ዓ/ም ጀምረው በመሰብሰብ የኛ ምልክት ‘ንብ’ ነው ፣ እኛን ምረጡ በማለት ህዝቡን በመቀስቀስ ደጋፊ ለማግኘት ባደረጉት እንቅስቃሴ በከተማችን አማራጭ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ባለመኖሩ ምርጫው ዴሞራሲያዊ ሊሆን አይችልም በማለት ህዝቡ ተቋውመውን መግለጹን ቷውቋል፣
        ባጋጠመው ተቃውሞ የተደናገጡ የስርዓቱ ካድሪዎች የከተማዋን ኗሪ ህዝብ ለማግባባት ሲሉ ተቋዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በሚደረገው ምርጫ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ስለሌላቸው እንጂ የከለከላቸው የለም በማለት ያቀረቡትን ምክንያት በከተማዋ ኗሪዎች በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘና ስብሰባውንም ረግጠው እንደወጡ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣