Sunday, March 8, 2015

የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ከየካቲት 14 እስከ 17/ 2007 ዓ/ም ከባድ ውጥረት የነገሰበት ግምገማ መካሄዱን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



   በደረሰን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የፖሊስ ኮሚሽን ዋና ፅህፈት ቤት አዳራሽ ከየካቲት 14 እስከ 17/ 2007 ዓ/ም ለተከታታይ 3 ቀናት ግምገማ መካሄዱ የገለጸው መረጃው ከክልሉ የተወጣጡ ከዋና ሳጂን በላይ ማዕረግ ያላቸው የፖሊስ አባላትን ያቀፈ “በክልላችን የሚገኘውን የአሸባሪዎች ፍሰት እንከላከል” በሚል አጀንዳ  ከባድ ውጥረት የነገሰበት ግምገማ እንደተካሄደ ለማወቅ ተችሏል።
   ከባድ እንደነበር በተነገረለት ግምገማም ላይ ለጊዜው ስማቸው ያልታወቀ ሁለት ንፁሃን የፖሊስ አባላት ህዝቡ ከፍተኛ ጥላቻ እያሳየን ባለበት ባሁኑ ሰዓት እናንተ ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት እያደረጋችሁ ናቹህ በሚል ተገምግመው መታሰራቸውን ምንጮቻችን አክሎው አስረድቷል።