Saturday, April 11, 2015

የባህርዳርና የደሴ ከተማ ነዋሪዎች። መንግስት ዘይትና ስኳር ገበያ ላይ ያቅርብልን ብለው በመጠየቃቸው ብቻ። አሸባሪዎችና አነሳሾች ተብለው እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በአማራ ክልል የደሴና የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወገኖቻችችን። በገበያ ላይ ስኳርና ዘይት ማግኘት ስላልቻሉና መንግስት ለምን ማቅረብ እንዳልቻለ ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ። የአሸባሪ ደጋፊዎችና አነሳሾች ተብለው እየተፈረጁና። በዚህም ምክንያት የደሴ 2ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ የነበረው አቶ ጌታቸው ተሰማ የተባለ ወገን ታስሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣
    በተጨማሪም። የባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆነውና በቅርብ ግዜ ከወታደርነት ስራ የተሰናበተው መጣለም ፀጋየ የተባለው ወገን። በተመሳሳይ መንገድ የዘይትና የስኳር አቅርቦት እጥረትን አስመልክቶ ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት ብቻ። በከተማው በ02 ቀበሌ ታስሮ እንደሚገኝና። የቀበሌው ነዋሪዎችም መፈታት አለበት በማለት አቤቱታቸውን እያቀረቡ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣