በመረጃው መሰረት። መጋቢት 3/2007 ዓ/ም
በምእራብ ዕዝ የሬድዮ መገናኛ ኦፕሬተር ምድብተኛ የሆነው ምክትል መቶ-አለቃ ኤብሳ የተባለው ወገን። ከተፈቀደው ሰዓት ውጭ ከጠላት
ጋር ተገናኝተሃል ተብሎ። በስርዓቱ ተላላኪዎች ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ታፍኖ እንደተወሰደና እስካሁን የት እንዳለ ለማወቅ እንዳልተቻለ
ተገልጿል፣
የክፍሉ የስታፍ አባላት ግለሰቡ ባልዋለበት ስራ ተወንጅሎ መታፈኑ ቢያስቆጣቸውም።
የኢህአዴግ የበላይ አዛዦች ግን። የተቃዋሚ ድርጅቶች በሰራዊቱ ውስጥ ገብተው ተደራጅተዋል በሚል ስጋት ምክንያት። የሚመሯቸውን የሰራዊቱ
አባላት በየግዜው በማፈን’ና በማሰር ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣