Saturday, April 11, 2015

ከሁሉም የገዠው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ወታደራዊ እዞች የሚከዳው ወታደር ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተገለፀ፣



በማዕከላዊ ዕዝ የ22ኛ ክፍለ ሰራዊት 4ኛ ሬጅመንት አባላት የሆኑ አስር አለቃ ሚጡ ቀሚሶና ወታደር ማለዳ በላቸው የተባሉ ወታደሮች ባለፈው መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም ሌሊት 8 ሰዓት ከቢያራ ሊከዱ ሞክረዋል በሚል ሁለቱም ሲገደሉ ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁ ሁለት ወታደሮች ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው። እንዳይታከሙም በከፍተኛ አዛዦች ተከልክለው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ከሰራዊቱ ውስጥ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
    እነዚህ ቆስለው በስቃይ ላይ የሚገኙ ወታደሮች ለምን አይታከሙም ሰብዓዊነት የጎደለው አሰራር ነው በማለት። በርካታ የሬጅመንቱ ወታደሮች የተቃውሙ ቢሆንም። እስካሁን ግን ሊሰማቸው  የሚችል አካል እንዳልተገኘና በተጨማሪም በአሃዱአዊ ስሜት በመነካት ወደ ስደትና ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች መቀላቀልና እየታየ ያለ መክዳት ከቀን ቀን ቁጥሩ እየተበራከተ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣
    በቅርቡም በምዕራብ ዕዝ የስታፍ አባል ሆኖ ይሰራ የነበረው አስር አለቃ ያሲን አህመድ ባለፈው መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ/ም ከጧቱ 2 ሰዓት ከክፍሉ እንደተሰወረና እስካሁን የት እንደሚገኝ አለመታወቁን ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣