Friday, April 10, 2015

ከሁመራ እስከ ትክል ድንጋይ ድረስ ያሉት የስርዓቱ ወታደሮች። ህዝቡን እያንገላቱት መሆናቸውን ምንጮች አስታወቁ፣



በመረጃው መሰረት። ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ አዲስ ወታደሮች ከሁመራ ጀምረው እስከ ትክል ድንጋይና ሌሎች አካባቢዎች ሰፍረው እንደሚገኙና። በተለይ በትግራይ ምእራባዊ ዞን ህዝቡ ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ እለታዊ ኑሮውን እንዳይመራ እንቅፋት ሁኖው እንደሚገኙ ተገለፀ፣
    መረጃው በማስከተል። እነዚህ ከስነ ምግባር ውጭ የሆኑ ወታደሮች በሴት እህቶቻችን ላይ ወሲባዊ አመፅ እየፈፀሙ ስለሚገኙ። በኤች አይ ቪ ኤዲስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች እየተጠቁ በመሆናቸው ምክንያት። ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለማሳደግም በመገደዳቸው ምክኒያት ነዋሪው ህዝብም ድርግቱ መፍትሄ እንዲደረግለት በማለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት ያቀረበውን ጥያቄ። እስካሁን መፍትሄ እንዳላገኘበት ለማወቅ ተችሏል፣