በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በወልቃይት ወረዳ
ማይ ገባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የስርአቱ ፌደራል ፖሊስ አባላት። ሰርተው ኑሮአቸውን የሚመሩ ዜጎቻችንን። የትጥቅ ትግል ለሚያካሂዱ
ድርጅቶች የተላካችሁ ናችሁ፤ በረሃ ላይ የደበቃችሁትን መሳሪያም አስረክቡን በማለት። መጋቢት 1/2007 ዓ/ም ለበርካታ ንፁሃን
ወገኖች በገመድ አስረው እየደበደቧቸው መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው። ምንም አይነት ወንጀል ሳይኖራቸው ባስከፊ ሁኔታ
እየተደበደቡ የዋሉት በርካታ ወገኖች ቢሆኑም። በተለይ ወርቅ ለቀማ ላይ የነበሩትን 6 ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን። ከተደበደቡት ውስጥም የአስገደ
ፅንብላ ተወላጅ የሆነው ሓዱሽ ታፈር የተባለ ንፁህ ወገን። ወድያውኑ መሞቱን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣