እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ
የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች ለነዋሪው ህብረተሰብ መሰረታዊ አላቂ ነገሮችን ከመንግስት ማግኘት የምትችሉት ለሰማዕታት
ቤተሰቦች ገንዘብ ስትከፍሉ ብቻ ነው እያሉ በጅምላ እያስገደዷቸው እንደሚገኙና። በከተማዋ የሚገኙ የሰማዕታት ቤተሰቦች ግን እኛ
የሰማታት ቤተሰቦች አይደለንም እንዴ ከኛ ወስዳችሁ ‘ለማን ለመስጠት ነው እያሉ በመቃወም ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ፣
የከተማዋ ነዋሪዎች የሰማዕታት ቤተሰቦች የወሰዱትን አቋም በመደገፍ። ለስርዓቱ
ካድሬዎች ከሰማታት ቤተሰቦች ገንዘብ ወስዳችሁ ለማን ነው የምትሰጡት? እውነትነት ካለው በከተማችን ያሉት የሰማዕታት ቤተሰቦች ገንዘብ
አዋጡ ከሚባሉ በግንባር ቀደም ሊደገፉ ይገባል። ካልሆነ ግን በሰማዕታት
ቤተሰብ ስም ገንዘብ እየወሰዳችሁ ማንም ተቆጣጣሪ በሌለበት እንደለመዳችሁት ለግል ጥቅማችሁ ታውሉት አላችሁ በፍፁም አናምናችሁም
የሰማዕታት ቤተሰቦች እራሳችን ነን የምናግዛቸው እንዳሏቸው። የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣