Sunday, April 5, 2015

የኢህአዴግ ስርአት በመከላከያ ሰራዊት ሲያገለግሉ የቆዩትን ያለምንም እገዛ ያባረራቸው ወታደሮች። ተመልሰው ወደ ውትድርና እንዲገቡ እያስገደዳቸው እንደሚገኝ ተገለፀ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። የኢህአደግ ስርአት መሪዎች በሰራዊቱ ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች የወጡትን የቀድሞ ወታደሮች። መጋቢት 1/ 2007 ዓ/ም ከዚህ በፊት ሳትጠቀሙ ስለወጣችሁ ወደ ጎረቤት ሃገር ሶማሊያና ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ሂዳችሁ ኑፘችሁን የሚቀይር ገንዘብ ታገኛላችሁ የሚል የማታለያ ሃሳብ በማቅረብ። ተመልሰው ወደ ውትድርና እንዲገቡ በተለይም የመኮነንነት መአርግ ያላቸውን በግዴታ እየመዝገቧቸው እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣
   ወታደሮቹ። በባህርዳር ከተማ ምእዕራብ እዝ ዋና መምሪያና መኮድ በተባለው አካባቢ እየተመዘገቡ መሆናቸውና። በማይተገበር ቃል ተታልለው እየተመዘገቡ ካሉት መካከልም። ሃምሳ አለቃ ተመስገን መሰለ፤ አስር አለቃ እብስት ብስራት፤ አስራ አለቃ ገልታው ባይኮዳ የተባሉት እንደሚገኙባቸውና አብዛኛው የቀድሞ ወታደር ግን መጀመሪያ አባርራችሁ አሁን ምን ለውጥ ስላለ ነው ድጋሜ ወደ ውትድርና የምንገባው በማለት ጥሪዉን እንዳልተቀበሉት መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣