Sunday, April 5, 2015

በቃፍታ ሁመራ ወረዳ የሚገኙ ገበሬዎች የእርሻ መሬታችሁን ልትጠቀሙበት ከፈለጋችሁ ኢንቨስተር ሁኑ አለበለዚያ ትቀማላችሁ ስለተባሉ። በከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣



  በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ልዩ ቦታ ሩዋሳ በተባለ አካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች በህጋዊ መንገድ ተሰጧቸው ሲጠቀሙበት የነበረውን የእርሻ መሬት። ከናንተ ጋር እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ ኢንቨስተር ነን ብላችሁ ተመዝገቡ ካልሆነ ግን ለኢንቨስተሮች እንሰጠዋለን ሲሉ የስርዓቱ አስተዳዳሪዎች መጋቢት 13/2007 ዓ/ም ስለነገርዋቸው። በከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣
     እነዚህ ገበሬዎች ኢንቨስተር ለማለት የሚያስችል አቅም የለንም መሬታችንን ከወሰዳችሁት ቤተሰቦቻችንን በምን እናስተዳድራለን በማለት ሃሳብ ባቀረቡበት ሰዓት የስርዓቱ ካድሬዎች እኛ የምናወቀው ነገር የለንም ከፈለጋችሁ ኢንቨስተር ለመሆን የሚያበቃችሁ ነጥብ አሟልታችሁ ቀጥሉ። ይህንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን መሬት የመንግስት ስለሆነ መልቀቅ ነው ያለባችሁ ስላሏቸው። በህወሃት ኢህአዴግ ብልሹ አስተዳደር የደረሰባቸውን ችግር በምሬት እየገለፁ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣