Friday, April 3, 2015

ያለምንም ማቛቛሚያ ከመከላከያ ሰራዊት የተባረሩት የኢህአደግ ወታደሮች በኑሮ ውድነት በመቸገራቸው ምክንያት። በስርቆትና ሌሎች ተግባሮች ለመሰማራት እንደተገደዱ ተገለጸ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ አካባቢ። ለአመታት በኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተው ያለምንም ማቋቛሚያ የተባረሩት 4 መኮንኖች። መጋቢት 2/2007ዓ/ም 8።00 ሰአት ከለሌቱ በፍኖተ-ሰላም ከተማ ውስጥ በሌሊት ባንክ ሲዘርፉ ተያዙ በማለት ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣
  ሲሰረቁ ተገኝተዋል ተብለው ከታሰሩት መኮንኖች መካከል። አንዱ ምክትል መቶ አለቃ የኔሰው የተባለ ሲሆን። የተቀሩት ደግሞ ለግዜው ስማቸው እንዳልታወቁና። የኢህአዴግ ስርአት ሲንከራተቱ የቆዩት ወታደሮችን። ያለምንም እገዛ ካባ  ረፘቸው በኋላ። በሲቪል አለም ውስጥ እንደገቡ ኑሮአቸው በከፋ ሁኔታ ላይ ስለሚገኝ። ሳይወዱ ወደ አልተፈለገ መጥፎ ስራ እንዲገቡ እተገደዱ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣