እንዳምንጮቻችን
መረጃ መሰረት። የኦሆዴድ/ኢህአዴግ የተመሰረተበትን 25ኛው አመት ለማክበር መጋቢት 17/ 2007ዓ/ም በነቀምትና
አርጆ ከተሞች በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረግ እየተከበረ በነበረበት ስአት። ነዋሪው ህዝብ በዓሉን በመቃወም በቦታው ሊገኝ
ስላልቻለ። የስርዓቱ ካድሬዎች የፀጥታ አካላትን በማሰማራት ከመኖሪያ ቤቱ አስገድደው እያስወጡት በነበሩበት ጊዜ። ከዚህ ድርጅት
ተጠቃሚዎች አይደለንም በዓሉም ህዝቡን አይወክልም ዛሬ ይሁን ነገ አንወጣም ሲሉ በድርጅቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በግልፅ ይናገሩ እንደነበር
ለማወቅ ተችሏል፣
የተካሄደውን የኦሆዴድ/ኢህአደግ በዓል ህዝቡ እንዳይደግፈው በተቃውሞው
ላይ እጃችሁ ነበረበት የተባሉትን መምህራን። ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኝነት
አላችሁ፤ በከተማው ፀረ መንግስት ቅስቀሳ ታደርጋላችሁ ተብለው። ከ30 አመታት በላይ ሲገለገሉበት ከነበሩት የስራ ቦታ ተነስተው
ወደ ገጠር አካባቢ እየተመደቡ በመሆናቸው። መምህራኖቹ በስራቸው ላይ የስነ አዕምሮ ጫና እንደፈጠረባቸው። ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል፣
ይህ በንዲህ እንዳለ። በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ከፍላጎታቸው ውጭ 50 ብር ለኦሆዴድ/ኢህአደግ በዓል
አዋጡ መባላቸውን የገለፀው መረጃው። አናዋጣም ያሉት ሰራተኞችም። አስጊዎች ናቸው እየተባሉ የወር ደመወዛቸው እንዳይከፈላቸው በመታገዱ
ምክንያት። ለከባድ የማህበራዊ ቀውስ ተጋልጠው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣