በአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን እንዳገለፁት። በአፋር ክልል በራሕለ ወረዳ
ልዩ ስሙ ባዳ በተባለው አካባቢ ለሚገኝ የተቸገረ ማህበረሰብ። ለእርዳታ ተብሎ ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኘውን እህል። መሓመድ አሕመድ
የተባለው የወረዳው ባለስልጣን። ለፀጥታ ስራ እንጠቀምበታለን በማለት ከ60 ኩንታል በላይ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ተካፍሎ ለግል ጥቅሙ
እንዳዋለው የአይን እማኞችን መሰረት በማድረግ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣
መረጃው በማከል።
ለሆዱ አዳሪ የሆነውን የወረዳው አስተዳዳሪ ተግባር የታዘቡት የአካባቢው ነዋሪዎች። ለችግረኛው ህዝብ ተብሎ የመጣውን እህል ማሓመድ
አሕመድ አየር በአየር በመሸጥ ከባልደረበቹ ጋር ተካፍሎ በልቶታል በማለት ወደ ሚመለከታቸው አካላት ክስ ቢያቀርቡና። የፖሊስ አዛዦቹ
አስረነዋል ልናጣራው ነው እያሉ ቢሆኑም። ባለስልጣኑ ግን እንኳን
ሊያስረው ይቅርና የጠየቀው የህግ አካል እንዳሌለም መረጃው አክሎ
አስረድቷል፣