በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በሁሉም የአማራ
ክልል አካባቢዎች የምግብ ዘይት ከገበያ ጠቅልሎ መጥፋቱና። በተለይ
በባህርዳር ከተማ ህዝቡ። የምግብ ዘይት አሉ በተባሉ መደብሮች ላይ በውድ ዋጋ ለመግዛት
በሌሊት ሳይቀር ወረፋ ይዞ እያደረ ቢሆንም። አልቋል እየተባለ ሳያገኝ ወደ ቤቱ እየተመለሰ እንደሚገኝ ተገልጿል፣
የኢህአዴግ ስርዓት በአላቂ ነገሮች አቅርቦት እጥረት ምክንያት እየተሰቃየ ያለውን ህዝብ። በላዩ ላይ አመፅ እንዳያስነሳ በመስጋት። ዘይት በጅቡቲ ወደብ
ደርሷል፤ ብዛት ያላቸው መርከቦች እየተራፈፉ ናቸው፤ ካሁን በኋላ የዘይት ይሁን የስኳር እጥረት አያጋጥምም በማለት እየተናገር ቢሆንም.። በተግባር ግን እስከ አሁን ድረስ አንዳችም ለውጥ እንዳልመጣ የባህርዳር ነዋሪዎች
በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣