Wednesday, February 10, 2016

በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን የሚኖር ህዝብ በሙስና ምክንያት ለ117 የመንግሰት ሰራተኞች በህግ ይጠየቁ በሚል ክስ እንደቀረበባቸው ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለጹ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣ በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን በሙስና አሰራር ምክንያት በህዝብ ላይ ያልተፈለገ ኪሳራ ሲያወርዱ የቆዩትን 117 የመንግስት ሰራተኞች፣ ነዋሪው ህዝብ በህግ ይጠየቁልን የሚል ክስ ለማቅረብ እንደቻለ ለማውቅ ተችሏል።
 በገዢው ሰረአት ለ25 አመት ያህል ሲከተለው በቆዩው ብልሹ አስተዳደር  አስራር ምክንያት ሊወጣው ወደማይልበት ውጥረትና መጨናነቅ ውስጥ እንደገባ የሚታውቅ ሆኖ፣ ይህን ማደናገሪያ ለማለፍ በዚህ አመት የተያዙ የስልት መድረክ የመልካም አስተዳደር የሚል ተደጋጋሚ ሰብሰባዎች በማካሂድ ለመልካም አስተዳደር ችግር ጠንቅ፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች የሚባሉ ሰዎችን  እርምጃ ወስዶ ለውጥ ለማምጣት በመድረክ እየፎከሩ ቢሆኑም፣ ይሁን እንጂ የተመጣጠነ ህጋዊ እርምጃ ሳይውስድ ሸፍነው ሊያልፉ እየሞክር እንዳሉ የገለፀው መረጃው፣ በችግሩ ተጎጂ የሆነውን ህዝብ በበኩሉ እውነትነት ያለው ማስረጃ በማቅረብ ተመጣጣኝ የሆነውን የየማስተካከያ እርምጃ ይውሰድ በማለት ድምፃቸውን በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።
መረጃው አክሎ እንደ ገለፀው፣  በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን    ህዝብን በሙስና ምክንያት ሲያስቸግሩ የቆዩትን የመንግሰት ሰራተኞች፣ እነዚህ ወንጀለኞች በህግ ይጠየቁልን ብሎ ካቀረበ በኃላ፣     ሃቅ ግን ህዝቡን እንዳልበራለት ከገለፀ በውኃላ፣  የመንግስት ሰራተኞችም በበኩላቸው ምን አድርጉ ትሉናላችሁ ሙስና ዋና የበላ የመንግት ከፍተኛ አመራሮች እያሉ እነሱን ሳይጠየቁ ከታች ለሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ ተጭነህ ሰተትን ማቅረብ አንቀበለውም በማለት ከባድ ግርግር እንደተፈጠረ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment