Wednesday, February 10, 2016

በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን በተካሄደው የመምህራን ስብስባ ላይ። በትግራይ ውስጥ የትምህርት ጥራት ባለመኖሩ ምክንያት ተማሪዎች ክፍል መቁጠር ብቻ ሆኖዋል የሚል ግምገማ ማካሄዳቸው ተገለፀ።



በምንጮቻችን መርጃ መሰረት፣ በትግራይ ምእራባዊ ዞን በተካሄደው የመምህራን ስብስባ በትግራይ ውስጥ የትምህርት ጥራት  ባለመኖሩ ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት የሚገቡ ተማሪዎች እውቀት  ከመገብየት ይልቅ ክፍሎችን መቁጠር ብቻ ሁነዋል በማለት መገምገማቸውን ምንጮቻችን ከአከባቢው የላኩትን መረጃ አሳውቀዋል።
 መረጃው ጨምሮ እንዳመለከተው፣ በአገራችን በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል የትምህርት ጥራት የሚባል ነገር እንደሌለና ውጤት ተኮርና በሌሎች ምክንያት አንድ መምህር ለምያስተምራቸው ተማሪዎች፣ ብቃት አግኝተው ሊያልፉ ሳይሆን በሚያስተምርበት ክፍል ተማሪዎች እንዳይወድቁበት ብቻ  የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ሊያሳልፋቸው  ሰለሚገደድ፣  ለደርጃቸው  የሚመጥን እውቀት ሳይዙ ክፍሎችን በመቁጠር ሰለሚያልፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከደረሱ  በኃላ፣  እንዲወድቁና በትምህርታቸው ሰነፎች  በመሆን ለተለያዩ  ማህበራዊ ኪሳራዎች  በመጋለጥ ወደ ስደት ሊያመሩ ምክንያት እንደሚሆንባቸው ለማወቅ ተችሏል። 

No comments:

Post a Comment