በደረሰን ዘገባ መሰረት በስርዓቱ የመከላከያ ሃይል ባሉ የተለያዩ ክ/ጦሮች ውስጥ በርካታ
ወታደሮች ባደረባቸው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ጭንቀት ምክንያት እራሳቸውን ያጠፉ ሲሆን ሌሎች 20 የስርዓቱ ወታደሮች ደግሞ ባደረጉት
እራስን የመግደል ሙከራ ቆስለው ከሞት ተርፈዋል ፣ ቁስለኞቹ በአሁኑ ግዜ ዓዲ-ኮኽብ በተባለ አከባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል
ተኝተው በመታከም ላይ ይገኛሉ ፣
በተለያዩ ክ/ጦሮች ባደረጉት እራስን የመግደል ሙከራ ቆስለው ከሞት የተረፉና በህክምና የሚገኙ
ወታደሮች ቁጥር።-
1-ከ 35ኛ ክ/ጦር-----6 ወታደሮች
2-ከ 33ኛ ክ/ጦር-----3 ወታደሮች
3-ከ 31ኛ ክ/ጦር-----4 ወታደሮች
4-ከ24ኛ ክ/ጦር-----5 ወታደሮች
5-ከ22ኛ ክ/ጦር-----2 ወታደሮች
በድምሩ 20 ወታደሮች ሲሆኑ በስርዓቱ ሰራዊት ውስጥ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን
እራስን የመግደልና የማቁሰል ተግባር እስካሁን ድረስ መፍትሄ ስላልተገኘለት አሁንም ቢሆን በከፋ መልኩ እየቀጠለ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል
፣