በደረሰን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተማዎችና
በወረዳዎች እንዲሁም በቀበሌዎች ሲሰሩ የቆዩ የኢህአዴግ አባላት በስልጣን ላይ ያለው የገዢው ሰረአት የፓለቲካ አካሂድ ይዞት ካለው
ሁኔታ አሰፈላጊ ሆኖ ባለመገኘታቸው ያለምንም ክፍያ የተለያየ ምክንያት
በመፈጠር እየተባበሩ ባለበት ግዜ ሰርተው የሚበሉበት እና ሌላ አማራጭ ሰራ የሚሆን መቋቋሚያ ገንዘብ ባለመሰጠታቸው ለከፋ የማህበራዊ ኑሮ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን
በደረሰን መረጃ ሊታወቅ ተችሏል።
እነዚህ የኢህአዴግ አባላት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሰዎች ለምንድነው ለብዙ
አመታት ከርተት ያልንበት ስራችንና አባልነታችን ተነጥቀን ያለምንም ክብር ተባረርን የሚል ጥያቂ ቢቀርቡም ተገቢ መልስ የሚሰጥ
አካል ባለማገኘታቸው የተነሳ። በሰረአቱ ላይ ከፋተኛ ሰሜት ይዘው እንደሚገኙ ምንጮቻች ገለፁ።