Wednesday, July 15, 2015

በኦሮሚያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞንና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች ማዳበርያ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አልቻልንም ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በማሰባቸው እየታሰሩ እንደሆኑ ተገለፀ።



    በመረጃው መሰረት በኦሮሚያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞን፤ ኖኖ ወረዳና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ-አደሮች በያዝነው  ዓመት ውስጥ መንግስትን ሁሉንም አርሶ-አደር በሚጠቀምበት መንገድ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበርያ ልያቀርብልን አልቻለም በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በመጠየቃቸው ብቻ 15 የሚያህሉ አርሶ-አደሮች አነሳሾች ተብለው መታሰራቸውን ታወቀ።
   ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቂያቸውን ስላቀረቡ ብቻ በስርዓቱ እንደ ጠለት ታይተው ከታሰሩት አርሶ-አደሮች መካከልም ክብረቴ ዳርጌ፤ ደብለው ቢተው፤ ፍቃዴ ደሳለኝና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።