በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ ባሶሊበን፤ ጎዛመንና
ደብረ ኤልያስ በተባሉ ወረዳዎች የሚገኙ የመሰናዶ ተማሪዎች ከታህሳስ 23/2007 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት መልካም እስተዳደርን
አስመልክቶ በተካሄደው ስብሰባ ተማሪዎቹ መድረኩን ረግጠው መውጣታቸው ተገለፀ።
መረጃው በማስከተልም መድረኩን ረግጠው ለመውጣት ያነሳሳቸውን ምክንያት ሲገልፅ
- መንግስት ነጋ ጠባ የትምህርት ጥራትን አስመልክቶ
ቢናገርም በተግባር ግን ጤነኛ የትምህርት ሁኔታ ማረጋገጥ አልቻለም፤
- በክልሉ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ በምስራቅ
ጎጃም ዞን ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ስራ የተሰማሩ ወጣቶች በጣም አንስተኛ ናቸው፤
- በወረዳችን ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን
የሚደረገው ጥረትና የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ እጅግ ደካማ ነው፤
- ለምርጫ ተብሎ እንጅ ከዚህ በፊት እንደዚህ
ዓይነት መድረክ ተከፍቶ እያውቅም ወ.ዘ.ተ በማለት ስብሰባውን እንዳልተቀበሉት መረጃው አስታውቋል፣
ከአማራ ክልል ሳንወጣ የምእራብ ጎጃም ዞን ወጣቶች የተቃዋሚዎች አባላት
እየተባሉ በስርዓቱ ካድሬዎች ታድነው እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ከአካባቢው ገልፀዋል።
በምእራብ ጎጃም ዞን ማንኩሳ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ከግንቦት 7 ድርጅት
ጋር ትተባበራላችሁ ተብለው እየታሰሩ መሆናቸውንና ታህሳስ 16/2007 ዓ/ም ሁለት ንፁሃን ወጣቶች ከቤታቸው ታስረው በመወሰድ ወደ
ፌደራል ተልከዋል ከተባሉ በኋላ እስካሁን ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንደማያውቁ ያገኘነው መረጃ አስታውቋል።
የገዢው ቡድን ባለ ስልጣናት በመገናኛ ብዙኃናቸው ነጋ ጠባ ከተቃዋሚዎች
ጋር ትገናኛላችሁ እያሉ የሚለፈልፉት ህዝቡን ለማደናገርና የአለምን
ማህበረሰብ ለማሞኘት የሚጠቀሙበት እኩይ ተግባር እንደሆነ ይታወቃል።