Sunday, October 13, 2013

በጎንደር ከተማ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መስከረም 26,2006 ዓ/ም ሞተው መገኘታቸው ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣




በደረሰን ዘገባ መሰረት በጎንደር ከተማ በተለምዶ አራዳ እየተባለ በሚጠራው አክሱም ሆቴል አከባቢ መስከረም 26,2006 ዓ/ም ሌሊት ገዳያቸው ያልታወቁ ምክትል ሳጅን ይፍጠር ዓሊና ምክትል ሳጅን ደምመላሽ ይርዳው የተባሉ ሁለት የፌደራ ፖሊስ አባላት ሞተው ተገኝተዋል፣ ከሟቸቹ አንዱ በጩቤ ተወግቶ የተገደለ ሲሆን በሁለተኛው ላይ በዓይን የሚታይ አካላዊ ጉዳት አልነበረውም፣ ታጥቀውት የነበረውንም ትጥቅ በገዳዮቹ መወሰዱን ቷውቋል፣
በስርዓቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት የሚደርሰው ጥቃት በሁሉም የሃገሪቱ ከተሞች የሚታይ ሲሆን በጎንደር ከተማ በሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት የደረሰውን ግድያ በኢህአዴግ ስርዓት በተማረሩ የስርዓቱ ኗሪዎች የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ በከተማዋ በሰፊው ይወራል፣