በሸራሮ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንት ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን ድረስ የተደረገ መፍትሄ
የለም፣ በዚሁ ምክንያት በከተማዋ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ለኗሪው አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ
ያመለክታል፣
በተመሳሳይ የመቆራረጥ ችግር የነበረበት የሞባይል ኔት ወርክ አገልግሎት በሁኑ ጊዜ በከተማዋ ሙሉ በሙሉ
አገልግሎት መስጠት አቁማል፣ በከተማዋ የውሃን አቅርቦት ችግርን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦት ችግር በህብረተሰቡ
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው፣