Wednesday, January 1, 2014

በቅርብ ግዜ ከሳውዲ አረብያ ለተመለሱ የትግራይ ተወላጆች በመንግስት ደረጃ ምንም አይነት ድጋፍ ስላልተደረገላቸው ተቸግረው እንዳሉና ለመጥፎ ሁኔታ እንደተጋለጡ የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣




በመረጃው መሰረት እነዚህ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን፣ የሳውዲ አረብያ መንግስት በራሱ ወጪ ወደ አገራቸው ቢመልሳቸውም፣ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ግን ለነዚህ  ከስደት ተመላሽ  ወገኖቻችን፣ አስፈላጊውን አቀባበልና የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት በገባላቸው ቃል መሰረት መተግበር ባለመቻሉና፣ አዲስ አበባ እንደደረሱ ግዚያዊ መጠለያና ማረፍያ ከማግኘታቸው በስተቀር፣ ትግራይ ውስጥ እንደገቡ የተደረገላቸው አንዳች የመንግስት ድጋፍና እገዛ ባለመኖሩ፣ ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣

          እስካሁን ድረስ የስርአቱ ባለስልጣናት በተለያዩ መድረኮች እንደግፋቹሃለን ብለው ከመናገር በስተቀር፣ በተግባር የሚታይ ድጋፍ ሲያደርጉ አላየንም ያሉት ተመላሽ ስደነኞቹ፣  በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ከገቡ በኋላ፣ ለስራ መነሻ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በጠየቁበት ሰአት በእርዳታ መልክ የሚሰጣቸው ገንዘብ እንደሌለና፣ ተደራጅተው ዋስ በማስመጣት ለአንድ ሰው 5ሺ ብር በብድር መልክ መውሰድ እንደሚችሉ ቢነገራቸውም፣ ይህን ለማስፈፀምም ውጣ ውረዱ በዝቶባቸው በጭንቀት ላይ እንዳሉ የተገኘው መረጃ አክሎ አስርድተዋል፣