በምንጮቻችን መረጃ መሰረት
በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙት ከ350 ሺህ በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል 240 ሺህ ተማሪዎች በ23 ዩኒቨርስቲዎች ከነሃሴ
10/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ ባቅራቢያቸው በሚገኝ ካምፓስ መገኘት እንዳለባቸው ትዕዛዝ እንደወረደ ታውቋል።
ይህ በአስቸኳይ እንዲገኙ የወረደ መመሪያ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ
እና የመልካም አስተዳደር መርህ ያለተገኘ ተማሪ በመደበኛ ትምህርቱ ሊገባ እንደማይችል የሚያመለክት ሲሆን ይህንን ተከትሎም ሳንወድ እየተገደድን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባል እንድንሆን
መደረጉ አግባብነት የለውም በማለት ቅሬታቸውን እያሰሙ መሆኑን አስረድቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ለነሃሴ 10 2006 ዓ/ም በአዲስ አበባ አራት
ኪሎ፤ ስድስት ኪሎና በሌሎችም ክልሎች ይጀመራል ተብሎ የነበረ ስብሰባ ባልታወቀ ምክንያት ለነሃሴ 15/ 2006 ዓ/ም እንደተራዘመና
ሁለተኛው ዙር ደግሞ ከነሃሴ 30/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚቀጥል መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።