Monday, September 22, 2014

ያገራችን ወጣቱ ሃይል ዋነኛው የለውጥ ሃወርያ ነው!!



   የማንኛውም አገር ሰላምና እድገት የሚረጋገጠው መንግስት በሚያስቀምጠው ትክክለኛ ታክቲክና ስትራተጂ ብቻ ሳይሆን የተቀመጠውን እቅድ ጠቃሚነቱን ተረድቶና አገናዝቦ ወደ ተግባር ሊተረጉም የሚችል ወጣት ዜጋ ወይም የህብረተሰብ ክፍል ሲኖር ነው።
    ወጣቱ ሃይል የአገር እድገትና የህዝቡን ጥቅም ሊያረጋግጥ የሚችለውን ፕሮግራም ፈጥኖ የማወቅ ችሎታ ያለው፤ ለይስሙላ ተብሎ የሚፃፈውን ጽሁፍ በተገቢ መንገድ የሚያገናዝብ፤ ባጠቃላይ ለህዝቡ የረባ ጥቅም የማያስከብር ስርአትና አመራር በመቃወም በላዩ ላይ የጭቆና ቀንበር ሲጩኑበት አሜን ብሎ የማይቀበልና የእምቢ አልገዛም ድምፅ ከሚያሰማ የህብረተሰብ ክፍል ዋናውና የለውጥ ተዋናይ የሆነው አካል ነው።
    ባገራችን ውስጥ የሚገኘውን ፀረ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እከተለዋሎህ የሚለውን መስመር ለራሱና የተከታዮቹ ጥቅም የሚያስከበር እንጂ የአብዛኛው ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት የማያሟላ በመሆኑ በተለይ ወጣቱ ክፍል ሰላምና እድገትን አሳጥቶ በግሉ ጥቅም ብቻ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ከዳተኛውን ስርአት አስወግዶ የአብዛኛው ጭቁኑ ህብረተሰብ ጥቅም ሊያረጋግጥ የሚያስችለውን ስርአት ለማምጣት በተለያየ መንገድ ትግል ስያካሂድ ቆይተዋል።
    ባለፈው ሳምንት የወያኔ ኢህአዴግ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ማህበር ስም አስጠምቆ የጠፈጠፋቸውና ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሰበሰባቸው ወጣቶች ቀጣይ እንዲካሄድ በታሰበው አስመሳይ ምርጫ ላይ አጫፋሪዎች አዘጋጅቶ ለመቆየትና ድጋፊዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ተስፋ ለጣለባቸው ስራ አጥ ወጣቶች ለማዘጋጀት አልሞ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳታፊዎቹ ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎች አቅርበውለት የሚያሳፍርና ቀልድ የተሞላበት መልስ ሲመልስ ተስተውለዋል።
    በስብሰባው የተገኝቱን ወጣቶች ካነሱት ጥያቄዎች ከፊሉን ለማንሳት
-    የኢህአዴግ መንግስት በያመቱ በአስር ሺዎች ተመራቂ ተማሪዎች ከተለያዩ ዩንቨርሲቲዎችና ኮሎጆች ቢመረቁም ለተመራቂዎች የሚሆን የስራ ቦታ ማዘጋጀት አልተቻለም፣
-    መንግስት ባገራችን ውስጥ ያሉትን በስራ አጥነት ችግር የሚሰቃዩት ወጣቶች ብድር በመስጠትና ገበያ በማፈላለግ ላይ ድክመት አለው የሚሉና ሌሎችም ቁልፍ ጥያቄዎች ባነሱበት ግዜ
ሃይለማርያም ደሳለኝ- ትላልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎች በሚካሄድበትና ቀልጣፋና ተከታታይ እድገት በሚረጋገጥበት አገር ላይ በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቢመረቁም ስራ አይታጣም፤ 80 ሚልዮን ህዝብ በሚገኝባት አገር በየአመቱ 10 ሺና ካዛ በላይ ተማሪዎች ማስመረቅ በጣም አንስተኛ ብሎ መመለሱና ብድር በመስጠት ላያና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄዎችም እንዲህ ሲል ገልፀዋል፣ በመንግስት ደረጃ ምንም አይነት ብድር የመስጠት ችግር እንደሌለና ችግሩ የአድልዎና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት እንደሆነ፤ ገበያ በማፈላለግ ሁኔታ ላይም በጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የሚመረቱ እቃዎች ጥራታቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ነው ሲል አሳፋሪ መልስ ሰጥቶበታል።
    እቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ባንዳንዱ ላይ ትክክለኛ መልስ ሰጥቶበት አልፈዋል ስርአቱ በግቦ፤ በኪራይ ሰብሳቢነትና በእድልዎ የተጨማለቀ መሆኑን ገና ወደ ስልጣን ከወጣበት ማግስት ጀምሮ በሰፊው እየተጠቀመበትና አየሰራበት ያለ ርካሽ ተግባር መሆኑን ሁሉም ያገራችን ህዝብ ያውቀዋል፣ ችግሩም በስርአቱ እየደረሰ ያለውን በደል የማወቅና ያለማወቅ ጉዳይ ሳይሆን ስርአቱ ወደ ስልጣን ከወጣበት ማግስት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ህዝቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢ በሆነ መንገድ ባለ-መመለሱና ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ባቻ ነው። 
   ያገራችን ወጣቶች በፀረ ህዝብ ስርአቶች የተነሳ ባገራቸው ላይ አስከፊ የድህነት ንሮ እንዲያሳልፉ፤ ሳይማር ላስተማራቸው ድሃ ቤተሰብ እንዳያግዙ፤ ወደ ስደት እንዲያመሩና ባልተፈለገ ርካሽ ባህልና ልምድ ተጠምዶው እንዲውሉ ምክንያት የሆነው አገራቸን በተፈጠረው ብልሹ ስርአት መሆኑን የሚያጠያይቅ አይደለም።
    ለማጠቃለል።-የኢህአዴግ ስርአት መሪዎች ገነባነው የሚሉዋቸው ፋብሪካዎችና በውጭ ባለ ሃብቶች የተሰሩትን ድርጅቶች የህዝቡን ጥቅም ለማረጋገጥ ታስበው ሳይሆን የስርአቱ ባለስልጣኖች ከውጭ ባለሃብቶች ተስማምተው የወጣቱን ነፃ ጉልበት ለመመዝበርና ያገሪቱን አንጡራ ሀብት ወረው የግል ሃብታቸው ለማበልፀግ በማሰብ ብቻ ስለሆነ ግላዊ ለሆነ አስተሳሰባቸውና አልጠግብ ባይ አመለካከታቸውን ለመስበር በተለይ ያገራቸን ወጣቱ ሃይል ዋነኛው የለውጥ ሃይል ነውና አሁንም እንዳለፈው ታሪካዊ ግዴታውን በመፈፀም ላይ አስፈላጊ ሚናውን መጫወት ይገባዋል።