Sunday, June 11, 2017

በመረብ ለኸ ወረዳ 12 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ቋሚ ዘበኞች፣ እንደማንኛውም ሰራተኛ እረፍት እየተገባን የእረፍት መብታችንን ተከልክለናል ሲሉ ገለጹ።



ከአከባቢው ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው፣ በትግራይ ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ በሚገኙ 12 የወረዳዋ ት/ቤቶች በጥበቃ መልክ ተቀጥረው የሚሰሩ ወገኖች፣ አመት ሙሉ ያለእረፍት ሌት እና ቀን እየጠበቁ እንዳሉና፣ እረፍት ለማግኘት ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ አመልክተው፣ መልስ እንዳላገኙ አሳውቀዋል።
ለአመታት ያህል ሌት እና ቀን ያለእረፍት ቁመን መስራታችን በሕግ የሰፈረውን የሰራተኞች መብት በግልፅ የሚጥስ ነው የሚሉት እነዚህ ዜጎች ፤አስከትለውም  ጉዳያችን በተገቢው መንገድ ታይቶ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲደረገለት በመግለፅ፣  የሰው ጉልበት ያለአግባብ መበዝበዝ መቆም እንደሚገባዉ፣ ሰራተኞቹ ጨምረው ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment