Friday, October 24, 2014

በቃፍታ ሁመራ፤ አዲ ጎሹ ቀበሌ የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች አርሶ-አደሮች የዘሩትን የሰሊጥ ምርት ነጥቀው ፀረ ሽፍታ ብለው ባሰማሯቸው ታጣቂዎች አሳጭደው ለግላቸው እንደተጠቀሙበት ተገለጸ፣





  በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአዲ ጎሹ አካባቢ ከመንገድ በታች የሚገኘውን ሰፊ የእርሻ መሬት የዞኑና የወረዳዋ አስተዳዳሪዎች የደን አካባቢ ነው ብለው ቢከልሉትም፤ የአካባቢው አርሶ-አደሮች ግን ተለዋጭ መሬት እንዲሰጣቸው ጠይቀው ተገቢ መልስ ስላልተሰጣቸው ሰሊጥ ዘርተውበት ከበቀለ በኋላ፤ የዞኑና የወረዳው አስተዳዳሪዎች ቡቃያውን ለማጥፋት ብለው የአረም መድሃኒት በረጩበት ሰዓት ሊጠፋ እንዳልቻለና፤ መጨረሻ ላይ ዘሩ ከደረሰ በኋላ ግን ፀረ ሽፍታ ብለው ባሰማሩዋቸው ታጣቂዎች አሳጭደው ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ለማወቅ ተችሏል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በአስተዳዳሪዎቹ ተግባር የተቆጣው የአካባቢው ህዝብ፤ በላያቸው ላይ ከባድ ተቃውሞና ግርግር ማስነሳቱን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣