እነዚህ በክልሉ ምስራቃዊ
ዞን የሚገኙ የከተማው አስተዳዳሪዎች ለማስመስል ሲሉ በከተማው ያለውን የመሰረተ ልማት ችግር ለመፍታት ብለው ክህዝቡ የሰበሰብቱን
ገንዘብ በታሰበው መንገድ ሳያውሉ ለግል ድርጅታቸው ማሰሪያ እያዋሉት እንደሆኑ ነዋሪዎቹ የገለፁ ሲሆን የህዝቡን ገንዘብ እያጠፋፉት
ካሉትም የአዲግራት ከተማ ከንቲባ የሆነው አቶ ተስፋ-ልደት ደስታ ለስታድዮም ማሰርያ ተብሎ ከህዝቡ የተዋጣውን ከ 600 ሽህ ብር
በላይ ገንዘብ ስላጠፋፋው ህዝቡ ትልቅ ስሜት ውስጥ መግባቱን የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
መረጃው በማስከተል የከተማው አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ገንዘብን ለማትረፍ
ሲሉ ከኮንትራክተሮች ጋር በማበር ጥራት የሌለው ፕሮጀክት እንዲሰራ እያደረጉ መሆናቸውና ከፕሮጀክቱም ውስጥ በከተማው ማሃል የሚገኘው
ፒያሳ /ጅራ ፍየሪ/ ለህንፃ መስርያ የሚያስፈልጉ በቂ ሰሚንቶ ስላልተደረገበት ብዙም ሳይቆይ እየፈረሰ ነው ያሉት ያካባቢው ነዋሪዎች
ተጠያቂውም የከተማው ከንቲባ ከኮንታርክተሮች ጋር ተባብሮ ጉቦ በመቀበሉና በቂ ክትትል ስላልተደረገለት ነው በማለት በአስተዳደሩ
ላይ ያላቸውን ጥላቻ እየገለፁ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።