Friday, September 26, 2014

በናዕዴር አዴት ወረዳ ስር የሚገኙ የ4 ቀበሌ ነዋሪ ህዝብ የወረዳው አስተዳደር ስለ-ራቀባቸው መፍትሄ እንዲደረግላቸው ላቀረቡት አቤቱታ መልስ እንዳላገኙለት የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



    ከቦታው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በወረዳው ውስጥ የሚገኙት የአበባ ዮውሃንስ፤ ላዕላይ አእዱግ፤ ሰሪሕኻ ብላዕና ናትካ ብላዕ በሚባሉት ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖረው ህዝብ የአስተዳደር አገልግሎት ለማግኘት ሰመማ ወደ ተባለችው ከተማ ለመሄድ 6 ሰአት ያህል እንዲጓዙ ግድ ስለሚላቸው ለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት ብለው ወደ ሚመለከታቸው አካል ብሶታቸው ቢያቀርቡም አወንታዊ የሆነ መልስ እንዳለገኙ ለማወቅ ተችለዋል።
    የቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ወደ አክሱም ከተማ ቅርብ ወደ ሆነችው ወደ ላእላይ ማይጨው እንዲቀየርላቸውና ካልተፈለገ ወጪና እንግልት ለመዳን ብለው ከ 8 አመት በፊት ጥያቄያቸው ቢያቀርቡም እስካሁን ድረስ መፍትሄ ባለማግኘታቸው ምክንያት ብሶታቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ከቦታው ገለፁ።
    የሚመለከታቸው ያስተዳደር አካላት የህዝቡን ችግር በቅድምያ አይተው መፍትሄ ከማፈላለግ የግል ጥቅማቸውን በማስቀደም እየተከተሉት ያለውን የተዛባ አመለካከት አክሱም ከተማ ውስጥ ተሰብሰበው የሰነበቱትን የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጥያቄውን እስነስተውት እንደነበር ቢገለፅም የዞኑ አስተዳዳሪዎች ግን  ተቃውሞና ግርግር እንዳይነሳ በመስጋት እንዲስተካከል እንደተወሰነ አስመስለው መልስ መስጠታቸውን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።