Saturday, October 4, 2014

በቡሬ ግንባር የሚገኙ የገዢው ኢህአደግ ወታደሮች በመሪዎቻቸው ላይ የመግደል እርምጃ እየወስዱ እንዳሉ ከሰራዊቱ ሸልኮ የደረሰን መረጃ ገለጸ።



  በመረጃው መሰረት እነዚህ በቡሬ ግንባር የሚገኙ የስርአቱ ወታደሮች በተደጋጋሚ በመሪዎቻቸው  ኢሰብአዊ የሆነ ግፍ እየደረሰባቸው እንዳለ የገለፀው መረጃው በደል የደረሰባቸው ወታደሮች በሃላፊዎቻቸው ላይ የመግደል እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸው ተገለፀ።
መሪዎቻቸውን ከገደሉ ወተሃደሮች አንዱ የሆነው ወታደር ይታያል የተባለ ግለ ሰብ በሃላፊዎቹ ክትትልስር መሆኖን ካወቀ በኃላ መስከረም 14 2007 ዓ/ም ቲም መሪውን ጨምሮ 3ት ሃላፊዎቹን መግደሉ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።
   የስርዓቱ ወታደሮች በመሪዎቹ ላይ እያካሄዱት ያለውን የመግደል እርምጃ በቡሬ ግንባር ብቻ ሳይሆን በሁሉም የኢህአደግ ስራዊት ክፍለጦሮች እየታየ ያለ ተግባር እንደሆነ ምንጮቻችን ከቦታው ጨምረው አስረድቷል።