Saturday, October 4, 2014

የኢህአዴግ መንግስት ጀነራሎች መስከረም 5/ 2007 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ሳይረዳዱ ተከፋፍለው እንደወጡ ተገለፀ።



    ይህ በአዲስ አበባ ከተማ ከክፍለጦር አመራር ባላይ የተገኙበት የግምገማ መድረክ ከላይ እስከ ታች ያለውን የመከላከያ ሰራዊት ፅ/ቤት ውስጥ ሙስና መስፋፋቱና ማናቸውም የሚተገበሩ ስራዎች በብሄር፤ ባገር ተወላጅነትና በጉበኝነት እንደሚሰራ የገለፀው መረጃው ይም አሰራር ውስጣዊ ግንኝነታቸው እንዲከፋፈልና መረዳዳት በማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ከሰራዊቱ ስታፍ ፅ/ቤት ሸልኮ የደረሰንን መረጃ ገለፀ።
   ይህ በጄነራል ሳሞራ የኑስ፤ ስራጅ ፈጌሳና ሃይለማርያም ደሳለኝ የተመራው መድረክ ስብሰባው ጭንቀት በተሞላበትና ነፃነት በሌለው መንገድ እንዲካሄድ በተሞከረበት ወቅት በስብሰባው የተገኙት አመራሮች ለህዳሴ ግድብ ተብሎ ሲዋጣ የቆየውን ገንዘብ ስራ ላይ ሳይውል ጄነራል ሰዓረ ሞኮነን ተጠቅሞበታል፤ ገንዘቡን እንደተጠቀመበት የሚያውቀውን ወዲ ዓፋር ለተባለው አማካሪው ሚስጢር እናዳያወጣ ብሎ በርከት ያለ ገንዘብ ስጥቶታል፤ በመቀሊ ከተማ በ1.5 ሚልዮን ብር ቤት አሰርተዋል በማለት ሰዓረ መኮነንን በህግ ፊት ቀርቦ መጠየቅ እንዳለበት ሃሳብ ቢቀርብም በወቅቱ ለቀረበው ሃሳብ የሚደግፉና የሚፃረሩ አካላት በሁለት በመከፈላቸው ምክንያት ሁኔታው መፍትሄ ሳይደረግለት እንደተበተነ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።