Sunday, December 21, 2014

በአዲግራት ከተማ ነዋሪ ህዝብና አካባቢው በህወሃት ካድሬዎች የቀረበላቸውን የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ጥሪ ተቃውመው የቀሩ ሰዎችን ከ70 ብር በላይ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እየቀጧቸው መሆናቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ።



በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማና አካባቢዋ የሚኖረውን ድሃ ህብረተሰብ በየአመቱ በግዴታ ውጣ እየተባለ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በመስራቱ የተነሳ ማህበራዊ ህይወቱን ለመምራት እጅግ ተቸግሮ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው፤ በዚህ የተማረረው ህዝብ ቸግሮናል ብሎ በሚቀርበት ሰዓት የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በቅጣት መልክ ከ70 ብር በላይ እያስከፈሉት እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል።
    ከድሃው ማህበረሰብ በቅጣት መልክ የተሰበሰበ ገንዘብ በልማታዊ ስራዎች ሳይውል በሙስና የተጨለቁ በአካባቢው በሚገኙ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች እየተበላ መሆኑን ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል።