Thursday, February 5, 2015

በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን የምርጫ ምዝገባ የሚያካሂዱ ሰዎች ያለ አበል አንሰራም ስላሉ አደናቃፊዎች ናችሁ እየተባሉ በመታሰር ላይ እንዳሉ ታወቀ።



በትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን በሚገኙ ከተሞች ሁመራ፤ ማይ ካድራና ወልቃይት በምርጫ ጣቢያ እየሰሩ የነበሩ ሰዎች እየሰራንበት ላለነው አበል ክፈሉን ብለው በጠየቁበት ጊዜ አበል የለም ዝም ብላችሁ ስሩ ስለተባሉ ለምን የድካማችን ዋጋ አይከፈለንም በሚል ብሶታቸውን አቅርበው አወንታዊ ምላሽ የሚሰጥ አካል በማጣታቸው ምክንያት ስራቸውን ለማቆም እንደተገደዱ ታውቋል።
    በዚህ መሰረት በህወሃት ካድሬዎች የምርጫ አደናቃፊዎች በመባል አቶ ተስፋይ መኮነንና ወ/ሮ አብረሀት ገብረመድህን የተባሉት የሚገኙባቸው የወልቃይት ነዋሪዎች የ6 ወር እስራት እንደተፈደባቸው ምንጮቻችን ከአካባቢው ያደረሱንን መረጃ አመለከተ።