Thursday, February 5, 2015

በታሕታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ የፖሊስ አባላት የታሰሩ ቤተሰቦቻችሁን እንድንፈታላችሁ ጉቦ ክፈሉን በማለት ገንዘብ በመውሰድ ላይ እንዳሉ ተገለፀ።



   በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ አድያቦ ወረዳ የተመደቡት የፖሊስ አባላት ልጆቻችሁን ከእስር ቤት እንድንፈታላችሁ ከፈለጋችሁ  ጉቦ ክፈሉ እያሉ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ገንዘብ ከነዋሪው ህዝብ እየተቀበሉ እንዳሉ የገለፀው ይህ መረጃ ከነዚህም መካከል በዛግር ኮሚኒቲ ፖሊስ  ተመድቦ የሚሰራ ፖሊስ ብርሃነ መሓሪ ሲሆን ከአቶ ሃጎስ ታምሩ የተባለ ግለ ሰብ የታሰረ ልጃችሁን እፈታላችዋለሁ በማለት 2,000  ብር ጉቦ ተቀብሎ ሲያበቃ እስረኛውን ከእስር ሊፈታው እንዳልቻለ ለማወቅ ተችሏል።