Friday, February 20, 2015

በዳንሻ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ተላላኪ የሆኑ ሚሊሻዎች በአካባቢው ወጣቶች መሳርያቸውን እየተነጠቁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድቷዋል።



   በመረጃው መሰረት በትግራይ ምዕራባዊ  ዞን ዳንሻ ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ የታጠቁ የገዥው መንግስት ተላላኪዎች ትጥቃቸውን በአካባቢው ወጣቶች እየተቀሙ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው እነኚህ ወጣቶች ይህንን ተግባር እንዲፈፅሙ ያስገደዳቸውን ምክንያት ሲናገሩ የስርዓቱ ተላላኪ ሚሊሻዎች በህዝብ ላይ እያደረሱት ያለውን ግፍ በመቃወም መሆኑን ታውቋል።
   መረጃው ጨምሮም ትጥቃቸውን የተቀሙ ሚሊሻዎችም በስርዓቱ ሊደርስባቸው በሚችለው እስራትና ድብደባ ስለሰጉ ህይወታቸውን ለማዳን ወደ ክልል 3 እና ሌሎች አካባቢዎች እየሸሹ መሆናቸውና  ወጣቶቹ በበኩላቸው የገዥውን ብልሹ አሰራር በመቃወም ወደ ተለያዩ ጫካዎች እየገቡ መሆንናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።