Friday, February 20, 2015

ገዢው የኢህአዴግ ስርዓት ከህዝብ ገንዘብ ለመበዝበዝ ካለው ስስት የተነሳ አዲስ ያወረደው ፍትሃዊነት የጎደለውን ትእዛዝ የቃፍታ ሑመራ አርሶ አደሮች እንደተቃወሙት ተገለጸ።



    በትግራይ ምእራባዊ ዞን የቃፍታ ሑመራ አርሶ አደሮች መሬት በሚመለከት በገዢው የኢህአደግ ጉጅሌ የወረደው ሃላፊንት የጎደለውን አዲስ ትእዛዝ በመቃወም ሰለማዊ ስልፍ ማካሄዳቸውን የገለጸው መረጃው ትእዛዙም ለቀጣይ ክረምት 2007ዓ/ም ማንኛውም አርሶ አደር ለአንድ ሄክታር 20ሺ ብር እንዲከፍል የሚያስገድድ እንደሆነ ታውቋል።
   መረጃው በማከል ከ800 በላይ የሚሆኑት የበረከት ከተማ ነዋሪዎች ጥር 23/ 2007ዓ/ም እንዲሁም ከ900 በላይ የሚሆኑ የማይ ካድራ ነዋሪዎች ጥር 25 2007 ዓ/ም የወረደውን ትእዛዝ በመቃወም ሃይለኛ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውና አቶ ካሕሳይ አረጋይና አቶ ተስፋይ በሪሁ የተባሉት የሚገኙባቸው ወገኖች በስልጣን ላይ ያለው የኢህአደግ መንግስት ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ የህዝቡን ኑሮ ግምት ውስጥ አያስገባም ሲሉ በሰለማዊ ሰልፉ ላይ ምሬታቸውን እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል።