Thursday, April 16, 2015

በሁሉም የሃገራችን ከተሞች የሚኖር ህዝብ በአላቂ ነገሮችና የአስተዳደር ችግር ምክንያት እየተማረረ ስለሆነ በስርአቱ ላይ አመፅ እንዳያስነሳ በሚል ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት እንዳለ ተወቀ፣



      በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ምንጮቻችን እንዳስረዱት። ጉጅሌው የወያኔ/ኢህአዴግ ስርአት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እየተከተለ ባለው  የሰብአዊና ዴሞክራስያዊ የመብት ጥሰት፤ የኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም የስራ አጥነትና አላቂ ነገሮችን  ስርአቱ ከቃል ባለፈ የሰጠው አወንታዊ ምላሽ እንደሌለ ከገለፀ በኋላ። በይበልጥም በአሁኑ ጊዜ ከህዝብ ጋር ተፋጥጦ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣
      ስርአቱ በመጪው ግንቦት 16/2007ዓ/ም በሚካሄድው ሃገራዊና ክልላዊ የይስሙላ ምርጫ ላይ። በህዝቡ የሚነሳውን ህዝባዊ አመፅ ለማፈን በማለት፤ በተለይ ደግሞ ህዝብ በብዛት የሚኖርባቸውን ከተሞች በረካታ አዳዲስ የፌደራልና የክልል ፖሊሶችን አሰማርቶ በከፍተኛ ጥበቃ ላይ እንደሚገኝ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣