Tuesday, June 16, 2015

በባህርዳር ከተማ ሙህየ ሁሴንና በቀለ አትርሳው የተባሉ ንፁሃን ዜጎች ያለምንም ጥፋት መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።



    እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር ከተማ ውስጥ በስርዓቱ ታጣቂዎች እንዲታሰሩ የተደረጉት ንፁሃን ዜጎቻችን በርካታ ተማሪዎችንና የአርሶ አደር ልጆችን እየቀሰቀሳችሁ የትጥቅ ትግል ወደሚያካሂዱ ድርጅቶች እየላካችሁ ነው  በሚል መሰረት የሌለው ውንጀላ ሲሆን። እነዚህ ንፁሃን ዜጎችም ባህርዳር ቀበሌ 02  ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ እስታወቀ።
   በመርጃው በማከልም በአሁኑ ጊዜ የኢህአዴግ አመራሮች ህዝቡን በማሰርና አንዳንድ ግለሰቦችንም  በስውር የመግደል እኩይ ተግባራቸውን እየቀጠሉበት እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።